loading
እጥረት እንዲፈጠር ባደረጉ የነዳጅ አቅራቢ ተቋማት እና ዴፖዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለፀ፡፡

ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ከንግድ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ሰሞኑን በተፈጠረው የነዳጅ እጥረት ዙርያ ከማደያ ባለቤቶችና ከነዳጅ አቅራቢ ተቋማት ጋር  ምክክር አድርገዋል፡፡

ምክትል ከንቲባው በወይይቱ ወቅት የነዳጅ እጥረት የተፈጠረው ባለድርሻ አካላት  ሀላፊነታቸውን ባለመወጣታቸው ነው ብለዋል፡፡

ዘርፉ የረጅም ጊዜ መፍትሄ የሚሹ ችግሮች ያሉበት በመሆኑ የከተማው አስተዳደር፣ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ያካተተ ግብረ-ሃይል በማቋቋም ገበያውን በቋሚነት የማረጋጋት ስራ ይሰራል ተብሏል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ እንዳለው ከፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመሆን በከተማዋ ውስጥ ያሉትን በነዳጅ ማደያ ዴፖዎችን ላይ ፍተሻ ያካሂዳል፡፡

በማከማቻ ስፍራዎች በቂ ነዳጅ እያለ እጥረት የተፈጠረ በማስመሠል ህብረተሰቡን የሚያጉላሉና ችግር እየፈጠሩ ያሉ ማደያዎች እና የነዳጅ አቅራቢ ተቋማት ላይ የማያዳግም እርምጃ ይወሰዳል  ሲል የከንቲባ  ፅ/ቤት መረጃውን በድረ ገፁ አስፍሯል፡፡

በሌላ የፅህፈትቤቱ መረጃ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ የሪል ስቴት አልሚዎችን የሚፈትሽ ግብረ-ሀይል ተቋቁሟል፡፡

ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በትናትናው ዕለት ከሪል ስቴት አልሚዎች ጋር ባደረጉት ውይይት በዘርፉ የሚታዩትን የአሰራር ችግሮች የሚፈትሽ ግብረ-ሃይል እንደሚቋቋም እና የሪል እስቴት ዘርፉ የቤቶች ልማት ፕሮጀክት ደጋፊ እንደመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ ህጋዊ የሆኑትን እንደሚደግፍም አስታውቀዋል፡፡

የሚቋቋመው ግብረ ሀይል በዋናነት በሪል እስቴት ኢንዱስትሪው ላይ የሚታዩትን ችግሮች የሚፈትሽ ሲሆን ከፕላን፣ ከካርታ፣ ከሊዝ እና መሬትን በህገ-ወጥ መንገድ አጥሮ ያስቀመጡትን እንደሚፈትሽ አስታውቀዋል፡፡

ከንቲባው በመንግስትም በኩል ያሉ አስተዳደራዊ ችግሮች እንደሚፈተሹም  ጨምረው ገልፀዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *