loading
ከህግ ያፈነገጠው የአማኑኤል ወንድሙ ግድያ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 4 ፣ 2013   የኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብቶች ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ደንቢ ዶሎ ቄለም ወለጋ ዞን በግንቦት 3 2013 ዓም በ ፀጥታ ሀይሎች በአደባባይ ላይ የተገደለው አማኑኤል ወንድሙ ሞት እጅግ ጭካኔ የተሞላበት እና ከህግ ያፈነገጠ ነው ሲል ገልጸ፡፡ ኮሚሽኑ ሁሉንም አይነት ህገ ወጥነት የሞላባቸው ግድያዎችን እንደሚቃወም የገለፀ ሲሆን ሰላም አስከባሪ ሀይላት ሰላም በማስከበሩ ስራ ብቻ እንዲሰማሩ በመልክቱ አፅንኦት ሰቷል፡፡ የሚመለከታቸው አካላትም በጉዳዩ ላይ ተገቢውን ምርመራ በማድረግ ፍትህ መስጠት እንደሚኖርባቸውና ኮሚሽኑም በቅርብ ሆኖ እንደሚከታተል እና ለህዝብ እንደሚያሳውቅ በይፋዊ ፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *