loading
ከሶስት ዓመት በፊት በፅንፈኛው አሸባሪ ቡድን አይሲስ ሊቢያ ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ 34 ኢትዮጵያውያን አፅምን ማግኘታቸውን የሊቢያ ባለስልጣናት አስታወቁ

ከሶስት ዓመት በፊት በፅንፈኛው አሸባሪ ቡድን አይሲስ ሊቢያ ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ 34 ኢትዮጵያውያን አፅምን ማግኘታቸውን የሊቢያ ባለስልጣናት አስታወቁ

አርትስ 16/04/2011

የሊቢያ የወንጀል ምርመራ መምሪያ ባለስልጣናትን ዋቢ አድርጎ ሬውተርስ እንደዘገበው፥ ተይዞ መርመራ ሲደረገበት የነበረ የአሸባሪ ቡድኑ አባል የሰጠውን መረጃ መሰረት በማድረግ በተከናወነ ምርመራ ነው ኢትዮጵያውያኑ የተቀበሩበት የጅምላ መቃበር የተገኘው።

መምሪያው ያወጣው በድሮን የተቀረፀ ቪዲዮም ሲርጥ ተብላ በምትታወቀው የሊቢያ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ በሚገኝ እርሻ ውስጥ ነው የጅምላ መቃብሩ የተገኘው።

የኢትዮጵያውያኑ አፅም ተገቢው የህግ ስራ ከተከናወነ በኋላም ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ እንደሚላክም ባለስልጣናቱ አስታውቀዋል።

ኤፍ. ቢ ሲ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *