loading
ከአንድ ክፍለ ዘመን በኋላ የተጠየቀው ይቅርታ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 20፣ 2013 ከአንድ ክፍለ ዘመን በኋላ የተጠየቀው ይቅር ጀርመን በቅኝ ግዛት ዘመን በናሚቢያ ላይ የዘር ማጥት ወንጀል መፈጸሟን ባአደባባይ አምና በመቀበል ይቅርታ ጠየቀች፡፡

የጀርመኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሄይኮ ማስ በ20ኛ ክፍለ ዘመን መባቻ ሀገራቸው ናሚቢያን በቅኝ ግዛት በምታስዳድርበት ወቅት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን መግደሏን በማስታወስ የሀገሬው ሰዎች ይቅር እዲሏቸው ጠይቀዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አክለውም ናሚቢያዊያን ይቅር እንዲሉን መጠየቃችን ከሞራልና ከታሪካዊ ሀላፊነት አንፃር ተገቢ ነው ብለዋል፡፡

ጀርመን በወቅቱ በናሚቢያ ህዝብ ላይ ለፈጸመችው በደልና ወንጀል እንደማካካሻ የሚቆጠር 1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ ማቀዷም ተሰምቷል፡፡

በ30 ዓመታት ውስጥ የሚሰጠው ይህ ገንዘብ ሀገሪቱ ለጤናና ሌሎች የመሰረተ ልማት አገልግሎቶች የምታውለው ሲሆን የተጎጂዎቹ ማህበረሰብ አባላት ተጠቃሚ ይሆኑበታል ተብሏል፡፡

የናሚቢያ መንግስት ቃል አቀባይ ቢሮ ሁኔታውን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ጀርመን ለጥፋቷ ይቅርታ መጠየቋ እንደ መጀመሪያ ትክክለኛ ርምጃ ተደርጎ ይቆጠራን ብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *