loading
ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ ሲጓዝ የነበረ ባቡር አደጋ ደረሰበት

ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ ሲጓዝ የነበረ ባቡር አደጋ ደረሰበት

ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ ሲጓዝ የነበረ የዕቃ ማጓጓዣ ባቡር ከሃዲዱ ተንሸራቶ በመውጣቱ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

በመምሪያው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር አስቻለው አለሙ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት አደጋው የደረሰው ባቡሩ በዞኑ ፈንታሌ ወረዳ ኢላላ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ሲደርስ ከሃዲዱ በመውጣቱ ነው።

17 ፉርጎዎችን ይዞ ሲጓዝ የነበረው ይሄ ባቡር ሌሊት 9፡00 ሰዓት ላይ ከሐዲዱ ሊወጣ የቻለው በወቅቱ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ሃዲዱ በደለል በመሞላቱ መሆኑን ተናግረዋል።

ባቡሩ ሲጎትታቸው ከነበሩ ፉርጎዎች መካከልም ሶስቱ በአደጋው ከአገልግሎት ውጭ ሲሆኑ በሶስቱ ላይ መጠነኛ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።

ሌሎች ሰባት ፉርጎዎች ከሐዲዱ በመውጣት ሳይገለበጡ የቆሙ ሲሆን አራት ፉርጎዎች ደግሞ ባሉበት መቆማቸውን ያስረዱት ኮማንደሩ ፤በሰው ህይወት ላይ አደጋ አለመድረሱን አስረድተዋል።

በተለይ በዝናብ ወቅት ሃዲዱ በደለል እንዳይጎዳ የቅርብ ክትትል እንደሚያስፈልግ ገልጸው አደጋው በሐዲዱ ላይ ጉዳት በማድረሱ የአዲስ አበባ ጅቡቲ መስመር ላይ መስተጓጎል መፈጠሩን ጠቁመዋል።

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *