loading
ከዓለም የልማት ድርጅት ጋር የተደረገው የገንዘብ ስምምነት ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀረበ

አርትስ 19/03/2011

የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ መንግስት በመወሰድ ላይ ያሉትን ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎች ለመደገፍ በመጀመሪያ ዙር 1.2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በቅርቡአፅድቋል ተብሏል፡፡

ይህም 600 ሚሊዮን ዶላሩ በብድር ቀሪው 600 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ በእርዳታ መልክ የተገኘ ነው፡፡

በዚህም መሰረት 600 ሚሊየን ዶላሩን ለማፅደቅ አጭር መግለጫ ለምክር ቤቱ ቀርቦ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡

በተገኘው ገንዘብ ከሚሰሩ ፕሮግራሞች መካከል የመንግስትና የግሉ ዘርፍ አጋርነትን ማሳደግ፣ የሀይል አቅርቦትን ማቀላጠፍ እንዲሁም የቴሌኮም ዘርፉንተወዳዳሪነት ማሳደግ ይገኙበታል፡፡

ከአለም ባንክ የተገኘው የ600 ሚሊዮን ዶላር ብድር የስድስት አመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ38 አመት የሚከፈል ነው ብሏል  ሸገር ራዲዮ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *