loading
ከግብር ጋር የተያያዙ 14 አዳዲስና ነባር መመርያዎች ተሻሽለው ፀደቁ

ከግብር ጋር የተያያዙ 14 አዳዲስና ነባር መመርያዎች ተሻሽለው ፀደቁ

የገቢዎች ሚኒስቴር እና የገንዘብ ሚኒስቴር ከግብር ጋር የተያያዙ 14 አዳዲስና ነባር መመርያዎችን አሻሽለው በማፅደቅ ወደ ሥራ እንዲገቡ መወሰናቸው ተነግሯል፡፡

በገቢዎች ሚኒስቴር ከወጡት መመርያዎች ውስጥ፣ ከተከፋይ ሒሳብ የንግድ ትርፍ ግብር ቀንሰው እንዲያስቀሩ ኃላፊነት የተሰጣቸው ታክስ ከፋዮችን ለመወሰን የወጣው መመርያ አንዱ ነው፡፡

የንግድ ሥራ ከተቋረጠ በኋላ በተገኘ ገቢ ላይ ግብር ስለሚከፈልበት ሁኔታ በገቢዎች ሚኒስቴር መመርያ የወጣ ሲሆን፣ የታክስ ክፍያ ጊዜ ማራዘምን የተመለከተው ሚኒስቴሩ ካወጣቸው መመርያዎች ውስጥ የሚጠቀስ ነው፡፡

ከተከፋይ ሒሳብ ላይ ሁለት በመቶ የንግድ ትርፍ ግብር ቀንሰው እንዲያስቀሩ ኃላፊነት ከተሰጣቸው ድርጅቶችና መሥሪያ ቤቶች በተጨማሪ፣ ሰፊ የአገር ውስጥ ግብይት ላላቸው ግለሰብ ግብር ከፋዮች ኃላፊነቱን በመስጠት የሚሠራበት ይሆናል ነው የተባለው፡፡

በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል ከወጡት ስድስት መመርያዎች ውስጥ የቅድመ ግብር ክፍያ ሥርዓት አፈጻጸም፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ ስለሚሆንበት መመርያና የታክስ ከፋዩን ሀብት ስለመያዝና ስለመሸጥ የወጡት መመርያዎች ይገኙበታል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በታክስ አስተዳደር አዋጁም በድርጅቶችና መሥሪያ ቤቶች ላይ የተጣሉ አስተዳደራዊ ቅጣቶች እና የወንጀል ድንጋጌዎች ተፈጻሚ እንደሚሆኑም ማሻሻያዎቹ ላይ ተቀምጧል፡፡ ሪፖረትር እንደዘገበው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *