loading
ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋራ እራት መብላት ይፈልጉ ይሆን?

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋራ እራት መብላት ይፈልጉ ይሆን?

እንግዲያዉስ እራት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ተጋብዘዋል፡፡

ዶክተር አብይ ሸገርን የማስዋብ ፕሮጀክት ለመደገፍ ለቢዝነስ ባለቤቶች፣ የኩባንያ ሥራ አስፈጻሚዎች፣ዓለም አቀፍ ድርጅት ኃላፊዎችና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላትን፤እራት በጋራ እንብላ ብለዉ ጋብዘዋል፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት እንዳገኘነዉ መረጃ ሸገርን የማስዋብ ፕሮጀክት ለመደገፍና ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጋር ገበታ ለመቅረብ የእራቱ ዋጋ በሰው: 5ሚሊዮን ብር ነዉ ተብሏል ::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈዉ ሳምንት ለአምቦ ከተማ ልማት ሰዓታቸዉን ለጨረታ በማቅረብ ሰዐቱ በ5 ሚሊዮን ብር መሸጡና ለከተማዋ ልማት ገቢ እንዲሆን መደረጉ ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *