loading
ከጤና ልማት አጋሮች ጋር በመሆን “ጋሽሮ ” የሚል ኘሮጀክት በ27.6 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይፋ ተደረገ::

ጤናጥበቃ ሚኒስቴር ከጤና ልማት አጋሮችና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ ˝የጋሽሮ˝ የሆድ ትላትልና የብላሃርዚያ በሽታዎች ሥርጭት ማቋረጫ ኘሮጀክት ይፋ አድርጓል፡፡
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በድረ ገጹ እንዳስነበበው የኘሮጀክቱ የሥራ ዘመን ከነሐሴ 2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 2022 እ.ኤ.አ. ሲሆን ድጋፍ የተገኘው እንግሊዝ አገር ከሚገኘው ቻይልድ ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን መሆኑ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሐይጂንና የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳኜው ታደሰ ተናግረዋል፡፡
ኘሮጀክቱ በአራት አመት ቆይታቸው 27.6 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይፈጃል ተብሏል፡፡ የኘሮጀክቱ ትግበራ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በእንግሊዝ አገር የሚገኘው የተዘነጉ የሀሩራማ በሽታዎች የምርምር ተቋም እና ከክልል እስከ ቀበሌ ያሉ የመንግሥት እና የሕዝብ ተሳትፎ የሚሰራ ሲሆን ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ለኘሮጀክቱ ተግባራዊነት በቅንጅት የሚሰራ ይሆናል፡፡
ኘሮጀክቱ በአራት አመት ቆይታው የውኃ ፣የመፀዳጃ ቤት ሽፋንን አሁን ካለበት ደረጃ ከፍ ከማድረግ በተጨማሪም የማህበረሰብ የጤና የባህሪይ ለውጥ ማምጣት የሚሉትን አላማዎች ያነገበ ነው፡፡
ለኘሮጀክቱ ስኬታማነት በየደረጃው ያሉ የስራ ኃላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት በትኩረት መሥራት አለባቸው ተብሏል፡፡ ኘሮጀክቱ በደቡብ ክልል በወላይታ ዞን በአምስት ወረዳዎች ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *