loading
ከ46 በላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት የጎዳና ላይ ሩጫዎች ውጤት አስመዝግበዋል

ከ46 በላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት የጎዳና ላይ ሩጫዎች ውጤት አስመዝግበዋል

አርትስ ስፖርት 26/02/2011

በሣምንቱ መጠናቀቂያ ላይ በተለያዩ የአለም አገራት በተካሄዱ በርካታ የጎዳናና ማራቶን ሩጫ ውድድሮች ላይ ከ46 በላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተካፋይ በመሆን ውጤታማነታቸውን ማሳየትችለዋል፡፡ በኒውዮርክ ሲቲ ማራቶን፡- በወንዶች 1ኛ ለሊሳ ዴሲሳ፣ 2፡05.5፤ 2ኛ ሹራ ኪጣታ፣ 2፡06.01፣ 4ኛ ታምራት ቶላ፣ ሲያጠናቅቁ፤ በሴቶች 5ኛ ረሂማ ቱሳ 9ኛ ማሚቱ ዳስካ ጨርሰዋ፡፡በፈረንሳይ የዴስ አልፕስ ማሪታይም ማራቶን – በወንዶች 1ኛ አብርሃም ሙላው፣ 2፡07.50፤ በሴቶች ደግሞ 1ኛ ኑሪት ሽመልስ፣ 2፡31.42 በመሆን አጠናቅቀዋል፡፡ በደ/ኮርያ ሴኡል ማራቶን በወንዶች1ኛ አሰፋ መንግስቱ፣ 2፡08.11፤ 2ኛ ታሪኩ ክንፉ፣ 2፡08.19፤ 3ኛ አብደላ ጎበና፣ 2፡08.32 ታሪኩ በቀለ 7ኛ በመሆን ጨርሰዋል፡፡ በፖርቱጋል ፖርቶ ማራቶን – በወንዶች ፍቃዱ ከበደ 3ኛ፤አብርሃም ግርማ 5ኛ ሲወጡ ፤በሴቶች አበባ ተከወሉ ገ/መስቀል፣ 2፡30.13 1ኛ፤ መስከረም አበራ ሁንዴ፣ 2፡33.50 2ኛ ሁነው አጠናቀዋል፡፡ በቻይና ሃንግዡ ማራቶን እና ናንጂንግ ማራቶን፤በጣልያን ቶሪኖ ማራቶን፣ በደ/አፍሪካ ሶዌቶ ማራቶን እንዲሁም በአሜሪካ EQT ፒትስበርግ 10 ማይል ውድድሮች ድል ቀንቷቸዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *