loading
ከ550ሺ ብር በላይ የሚያወጡ እቃዎች በህገወጥ መንገድ ሊገቡ ሲሉ ተያዙ፡፡  

ከ550ሺ ብር በላይ የሚያወጡ እቃዎች በህገወጥ መንገድ ሊገቡ ሲሉ ተያዙ፡፡

ከሶማሌ ላንድ (ቶጎጫሌ) ወደ ጅግጅጋ ታህሳስ 23/2011 ዓ.ም የተነሱ ኮድ-04046፣ኮድ-05759 ሁለት ቅጥቅጥ አይሱዙ እና ኮድ-39416 የጭነት ተሸከርካሪዎች ግምታዊ ዋጋቸዉ ከ550ሺ ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ የኤሌክትሮኒስ፤ምግብ ነክ፣ጨርቃ ጨርቅ እና ሌሎች እቃዎችን ጭነዉ በህገወጥ መንገድ ወደ ጅግጅጋ ለመግባት ሲሞክሩ ተያዙ፡፡

በፌደራል ፖሊስ፣በጉምሩክ ሰራተኞች እና በክልሉ አድማ ብተና በተደረገ ከፍተኛ ክትትል የኮንትሮባንድ እቀዎቹ የተያዙት በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት ነዉ፡፡

የቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ደመላሽ ተሾመ እንደተናገሩት በድርጊቱ ተሳታፊ የነበረዉ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዉሎ አስፈላጊዉ ክትትል እየተደረገ ሲሆን ሌሎች ተጠርጣሪዎችንም በህግ ስር ለማዋል ቁጥጥሩ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል፡፡

አቶ ደመላሽ ህብረተሰቡ ይሄን መሰል ድርጊቶችን በንቃት በመከታተል ለህግ እንዲቀርቡ በማድረግ የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ ከገቢዎች ሚኒስቴር እንዳገኘነዉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *