loading
ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ካፒታል ስራውን የሚጀምረው አማራ ባንክ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2014 አማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር በሳምንቱ መጨረሻ ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር ይፋ አደረገ፡፡ ባንኩ በ6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር መነሻ ካፒታል ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ስራውን በይፋ እንደሚጀምር ነው ያስታወቀው፡፡

የባንኩን ስራ የመጀመር ሂደትን አስመልክቶ የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች መግለጫ ጋዜጣዊ ሰጥተዋል። በ6 ቢሊዮን 516 ሚሊዮን ብር በላይ በተከፈለ የመነሻ ካፒታል እንዲሁም ከ4 ቢሊዮን 825 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ገንዘብ ተጨማሪ አቅሙን በማሳደግ ባንኩ ለስራ ዝግጁ መሆኑን የባንኩ
የቦርድ ሊቀመንበር አቶ መላኩ ፈንታ ገልጸዋል።


በመነሻነት በ70 ቅርንጫፎች ስራውን የሚጀምረው አማራ ባንክ እስከ ሰኔ 30 ባለው ጊዜ ውስጥ የቅርንጫፎቹን ቁጥር ወደ 100 ከፍ ለማድረግ ማቀዱም በመግለጫው ተመልክቷል፡፡ ባንኩ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ባለ አክሲዮኖች ያሉት መሆኑንም ነው አመራሮቹ የገለጹት፡፡
ከመደበኛው የፋይናስ አገልግሎት በተጨማሪ “ከባንክ ባሻገር” በሚል የአገልግሎት ዘርፍ የማህበረሰቡን ሕይወት ለማሻሻል የተለያዩ አማራጮችን ማዘጋጀቱንም ተሰምቷል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *