loading
ካሜሮን የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ አሳስቦኛል አለች

ካሜሮን የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ አሳስቦኛል አለች

አርትስ 26/02/2011

በካሜሮን በርካታ የማእድን ማውጫ ስፍራወች እድሜያቸው ከ18 በታች የሆኑ ህፃናት ከአቅማቸው በላይ በሆነ ስራ ተጠምደው ማየት ብዙም እንግዳ ነገር አይደለም፡፡

ይህን ደግሞ በማዕድን ቆፋሮ ተግባር ላይ የተሰማሩ ሰወች ሳይቀሩ በኩራት ይናገሩታል፡፡ ጀስቲን እምራማ የተባለ ግለሰብ እነዚህ ህፃናት የወርቅ ማእድን  ፈልጎ በማውጣት ተካኑ ናቸው እኛም ብንሆን የተወሰነ ገንዘብ ስለምንሰጣቸው ተጠቃሚወች ናቸው ይላል፡፡

አፍሪካ ኒውስ በዘገባው የካሜሮን ህፃናት በድህነት ተገፍተው ሳይወዱ በግዳቸው በነዚህ የማዕድን ቁፋሮ ቦታዎች ተበትነዋል ሲል አስነብቧል፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህፃናት ጥበቃ ቢሮ በበኩሉ ጉዳዩ እንዳሳሰበው ደጋግሞ ቢወተውትም እስካሁን ጠብ ያለ ውጤት አልተገኘም፡፡

በድርጅቱ የህፃናት ጥበቃ ቢሮ ሀላፊ የሆኑት ባርባራ ጀማር እንደሚሉት በህፃናቱ ላይ እየደረሰ ያለውን ማህበራዊና ስነ ልቦናዊ ቀውስ ለመቀየር የሁሉንም እገዛ ይፈልጋል፡፡

የሀገሪቱ የሀይማኖት መሪዎች በበኩላቸው ልጆች ወደ ትምህርት ቤት እንጂ ጉልበታቸው ወደሚበዘበዝበት ቦታ መሄድ የለባቸውም በማለት ድምፃቸውን ቢያሰሙም መልስ አላገኙም፡፡

በዘቅተኛ ኑሮ የሚገኙት የህፃናቱ ወላጆችም ነገሩን እንደ አንድ የገቢ ምንጭ ስለሚቆጥሩት ለልጆቻቸው ከመቆርቆር ይልቅ እንደ መልካም አጋጣሚ ይቆጥሩታል ነው የተባለው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *