loading
ካጋሜ ከስነምግባር ጉድለት ጋር በተያያዘ 4 ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎችን ከስራ አገዱ

ካጋሜ ከስነምግባር ጉድለት ጋር በተያያዘ 4 ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎችን ከስራ አገዱ

አርትስ 16/02/11

ካጋሜ ከስነምግባር ጉድለት ጋር በተያያዘ ችግር አይቼባቸዋለሁ ያሏቸውን ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎችን ከስራ ማገዳቸው ተነገረ።

ኢስት አፍሪካን እንደዘገበዉ የሩዋንዳዉ ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ ብልሹ ስነምግባር ያላቸዉን 4 ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች ከስራቸዉ እንዲባረሩ አድርገዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ከስራ ያገዷቸዉ ሃላፊዎችም የእንስሳት ሃብት ማስፋፊያ ዳሬክተር ሲሪዲዮን ዱሳቢማና ፣ በሩዋንዳ ብሄራዊ ሙዚየም የፋይናንስና አስተዳደር ዳይሬክተር የሆኑት ማርጋሬት ባባዚ፤ በትራንስፖርት ልማት ኤጀንሲ የአስተዳደር ዳይሬክተሩ አልበርት ሩሁማ ሪዛ እና የአይሲቲ ዳይሬክተር የሆኑት ኢማኑኤል ቶቶ ዋ ሙጌንዛ ናቸዉ፡፡

ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ ከሁለት ወር በፊት የህዝብ ሃብት ያለ አግባብ አባክነዋል በሚል የጤና ሚኒስትሩን ከስራ ማገዳቸዉ ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *