loading
ኬንያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባልነት ምርጫን አሸነፈች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 12 ፣ 2012  ቢቢሲ እንደዘገበው ከአፍሪካ ሀገራት ኬንያ እና ጂቡቲ በተወዳሩበት ምርጫ ኬንያ ጂቡቲን 129 ለ62 በሆነ የድምፅ ልዩነት በማሸነፍ ነው የምክር ቤቱን መቀመጫ ያገኘችው፡፡የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጂቡቲን በብርቱ ተፎካካሪነቷ አድንቀው የአፍሪካ ህብረትን ደግሞ ለሀገራቸው ለሰጠው እውቅና አመስግነዋል፡፡ኬንያ ይህን ውድድር ማሸነፏ በአካባቢው ያላት ተሰሚነት ከፍ እያለ የመምጣቱን የሚያመላክት ነው ያሉት ኡሁሩ በምክር ቤቱ ቆይታችን የአፍሪካን ድምፅ ከፍ አድርገን እናሰማለን ብለዋል፡፡

ኬንያ በምርጫ ቅስቀሳው ወቅት የፓን አፍሪካን አጀንዳ በመጠቀም ዓለም ሰላም፣ አንድነት እና ወንድማማችነት እንዲሰፍን ጠንክራ እንደምትሰራ ቃል ገብታለች፡፡ኬንያ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣር ከ2021 እስከ 2022 ምክር ቤቱን በተለወጭ አባልነት ለማገልገል የተመረጡትን ኖርዌይ፣ አየርላንድ፣ ሜክሲኮ እና ህንድን ተቀላቅላለች፡፡ናይሮቢ በምስራቅ አፍርሪካ ብሎም በመላው አፍሪካ ሰላም እንዲሰፍን ጠንክሬ እሰራለሁ ያለች ሲሆን ደቡብ አፍሪካን ተክታ ነው የምክር ቤቱን ወንበር የምትረከበው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *