ኬንያ በአልኮል ወረርሽኝ ተጠቅታለች ተባለ
አርትስ28/01/2011
በፈረንጆቹ 2016 የወጣ ጥናት እንደሚያሳየው በአልኮል መጠጥ ሳቢያ ህይዎታቸው ሚያልፍ ኬንያውያን ቁጥራቸው በእጅጉ ጨምሯል፡፡
የሀገሪቱ ጋዜጣ ደይሊ ኔሽን እንደዘገበው ኬንያ ውስጥ ከሚመዘገብ 100 ሞት መካከል አራቱ ከአልኮል ጋር በተያያዘ ችግር መሆኑ በጥናቱ ተረጋጋጧል፡፡
በዓለም ጤና ድርጅት የተደረገው ይህ ጥናት እንደሚለው በተለይ ቻንጋ ወይም ኩሚ ኩሚ በመባል የሚታወቀው በባህላዊ መንገድ የሚጠመቅ የአልኮል ዓይነት ነው ትልቁ የሞት መንስኤ፡፡
በኬንያ አልኮል አብዝተው በመጠቀም ሳቢያ የጤና መቃወስ የሚደርስባቸው ሰዎች ከጠቅላላው የሀገሪ ዜጎች አራት በመቶ መሆናቸውንም ጥናቱ ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህም ምክንያት ኬንያ የአዕምሮ እና የህፃናት ጤናን በመጠበቅ እንዲሁም ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በመከላከል ረገድ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት ትቸገራለች የሚል ስጋት እንደገባው ድርጅቱ ተናግሯል፡፡