loading
ዋሊያዎቹ ከጋና አቻቸው ጋር ላለባቸው ጨዋታ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገላቸው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን /ዋሊያዎቹ/ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ህዳር 9/2011 ዓ.ም ከጋና ጋር ላለበት ጨዋታ ከጥቅምት 27/2011 ዓ.ም ጀምሮ ልምምዱን የሚጀምር ሲሆን 23 ተጨዋቾች የተመረጡ በመሆናቸው ጥቅምት 26 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በካፒታል ሆቴል ተገኝተው ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ተደርጓላቸዋል፡፡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ አስቻለው ታመነ፣ አብዱልከሪም መሐመድ፣ ሙሉዓለም መስፍን፣ አቤል ያለው እና ጌታነህ ከበደ ሲጠሩ፤ ከኢትዮጵያ ቡና ተመስገን ካስትሮ፣ አህመድ ረሺድ፣ ዳንኤል ደምሱ እና ሳምሶን ጥላሁን ተካትተዋል፡፡ ከመከላከያ አቤል ማሞ፣ አበበ ጥላሁን እና ምንይሉ ወንድሙ፤ ከድሬዳዋ ከነማ ሳምሶን አሰፋና አንተነህ ተስፋዬ ጥሪ ሲቀርብላቸው ከአዳማ ከተማ ከነዓን ማርክነህ፣ ከፋሲል ከነማ አምሳሉ ጥላሁን፣ ከሲዳማ ቡና አዲስ ግደይ፣ ከሀዋሳ ከተማ ደስታ ዮሐንስ እንዲሁም ከመቀሌ ከተማ አማኑኤል ገ/ሚካኤል ተጠርተዋል፡፡ ሽመልስ በቀለ ከፔትሮጄት/ግብፅ፣ ጋች ፓኖም ከኤል ጎውና/ግብፅ፣ ቢኒያም በላይ ከስከንደርቡ/አልባኒያ፤ ዑመድ ኩኩሪ ከ ስሞሀ/ግብፅ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *