loading
ዋልያዎቹ ከአፍሪካ ዋንጫ ውጭ ሆኑ
አርትስ ስፖርት 09/03/2011
በ2019 በካሜሮን አስተናጋጅነት ለሚካሔደው የአፍሪካ ዋንጫ፤ የምድብ አምስተኛ የማጣሪያ ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ ጋናው አቻው ጋር ተጫውቶ የ 2 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዷል ።
በጨዋታው የጋና ብሄራዊ ቡድን ( ጥቋቁር ድመቶቹ ) በመጀመሪያው አጋማሽ ከጨዋታ ብልጫ ጋር ጆርዳን አየሁ በጨዋታና በፍፁም ቅጣት ምት ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች እየመሩ ወደ መልበሻ ክፍል ለእረፍት አምርተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ ) ይህን ወሳኝ ጨዋታ በሜዳቸውና በደጋፊዎቻቸው ፊት ቢያደርጉም ከመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ ይልቅ በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ ለመንቀሳቀስ ሙከራ ቢያደርጉም፤ በጋና ጥንቃቄ የተላበሳ የጨዋታ እንቅሰቃሴ ተደምሮ ግብ ሲያስቆጥሩ በ2 ለ 0 ውጤት ተሸንፈዋል ።
በምድቡ የሴራሊዮን ብሔራዊ ቡድን ላይ የተጣለው እገዳ ቁርጥ ውሳኔ እስኪያገኝ ኬንያ ምድቡን በሰባት ነጥብ ሲመሩ ጋና በስድስት ነጥብ ሁለተኛ በመሆን ወደ አፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ የሚያደርጉትን ግስጋሴ አጠናክረዋል።
በመጨረሻ የምድቡ ጨዋታ ጋና ከ ኬንያ ይገናኛሉ።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *