loading
ዋልያዎቹ ዛሬ ከኬንያ አቻቸው ጋር የአፍሪካ ማጣሪያ ጨዋታን ያደርጋሉ

አሰርስ ስፖርት30/01/2011
በ2019 በካሜሮን አዘጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የምድብ የማጣሪያ ጨዋታዎች እየተካሄዱ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) በምድብ ስድስት ሶስተኛ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታን ከኬንያ አቻቸው ጋር በባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም ከቀኑ 10፡00 ስዓት ጀምሮ ይጫወታሉ፡፡
ከጨዋታው አስቀድሞ የሁለቱ ብሄራዊ ቡድኖች አሰልጣኞች ለጋዜጠኞች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
የኬንያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሰባስትያን ሚኜ፡ ሁለታችንም እኩል ቁመና፤ 50 በመቶ ላይ ነን እኛ ግን አሸንፈን 51ዱን እንሆናለን፤ ተጫዋቾቼንም ያገኘሁት ገና ሁለት ቀን ቢሆንም ለማሸነፍ መጥተናል፤ ሁለቱም ቡድኖች በማሸነፍ ጥሩ ስነልቦና ላይ ይገኛሉ፤ በእግር ኳስ ምን አንደሚፈጠር ባናውቅም እናሸንፋለን ሲሉ ተናረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ በሰጡት አሰተያየት፡ ተጫዋቾቻችን በተቻለ መጠን በፊዚካልም ሆነ በአዕምሮም እንዲዘጋጁ ተደርጓል፤ ኬንያ ትልልቅ ተጫዋቾች አሏት፣ ነገር ግን ተጫዋቾቼ ተገቢውን ክብር ይሰጣሉ፤ አቅልለውም አክብደውም እንዳያዩ በስነልቦናው ለማዘጋጀት ተሞክሯል ብለዋል፡፡ ሁለቱም ቡድኖች ጥሩ የማሸነፍ ስነልቦና ላይ ናቸው ሲሉ አክለዋል፡፡
አሰልጣኝ አብርሃም ከጉዳት ጋር በተያያዘ ሳላሃዲን እና በሀይሉ በጨዋታው እንደማይኖሩ አስቀድሞ ታውቋል ያሉ ሲሆን፤ አስቻለው ላይም የትናንትናውን ሳይጨምር ከሶስቱ ቀን በፊት በነበረው ሙሉ ልምምድ ሰርቶ ነበር ነገር ግን ዛሬ የህክምና ባለሙያዎች የሚሉትን አድምጠው እንደሚወስኑ አስታውቀዋል፡፡ ናትናኤልም በጉዳት ዘግይቶ ልምምድ የጀመረ በመሆኑ ዛሬ በጨዋታው ስለሚኖረው ሚና እወስናለሁ ብለዋል፡፡
በምድብ ስድስት ሁሉም ቡድኖች ተመሳሳይ ሶስት ነጥብ የያዙ በመሆናቸው ፉክክሩን አጓጊ አድርጎታል፡፡
ከሴራሊዮን ብሄራዊ ቡድን ጋር በተያያዘ ከጋና ጋር ለሚኖረው ጨዋታ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ስዓት ድረስ እየወጡ ባሉ መረጃዎች ጨዋታው እንደማይደረግ በፊፋና ካፍ እገዳው ተላልፏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *