ዋሽንግተን ካርቱምን ከሽብርተኞች መዝገብ ለመሰረዝ ዝግጁ ናት ተባለ
አርትስ 06/03/2011
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን መሰረት አድርገን ለመስራት ቁርጠኛ አቋም አለን ብሏል፡፡
አሜሪካ ሱዳንን ከሽብርተኝነት ዝርዝር ለማውጣት የሚያስችላትን ሂደት ለመጀመር ተዘጋጅታለች ያሉት ደግሞ በሱዳን የአሜሪካ አምሳደር ስቴቨን ኮትሲስ ናቸው፡፡
አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው ሱዳን በሽብርተኝነት ዝርዝር ውስጥ መግባቷ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ብድር እንዳታገኝ እንቅፋት ሆኖባት ቆይቷል::
ሱዳን በበኩሏ የተገባላት ቃል እንዲፈፀም እና ቀጣይነት እንዲኖረው የሰብዓዊ መብት አያያዟን ማሻሻል ይጠበቅባታል ነው የተባለው፡፡
ካርቱም በሽብርተኞች ዝርዝር እንድትካተት የተደረገችው በፈረንጆቹ ከ1992 እስከ 96 ባለው ጊዜ ውስጥ የቀድሞውን የአልቃኢዳ መሪ ኦሳማ ቢን ላደንን አስጠግታለች ተብላ መሆኑ ይታወሳል፡