loading
ውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ለ1ሺ ሰዎች ነፃ ምርመራ ሊያደርግ ነው ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 20፣ 2012 ውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ለ1ሺ ሰዎች ነፃ ምርመራ ሊያደርግ ነው ::ውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ የጤና ምርመራዎችን ከፍለው መመርመር ለማይችሉ 1ሺህ ሰዎች በነፃ ምርመራ ሊያደርግ መሆኑን ገልጿል፡፡

ማዕከሉ˝ጳጉሜን ለጤና˝ በሚል ዘመቻ ላለፉት አስር አመታት ከተለያዩ አገሪቱ ክፍሎች ለሚመጡ ታካሚዎች በነፃ ምርመራ የሚያደርግ ሲሆን ከዚሁ ጎን ለጎንም በምርመራ ውጤት ለሚገኙ ህመሞች ህክምና እና መድሃኒት ለህሙማን ማቅረቡን ማዕከሉ ለአርትስ ቲቪ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ዘንድሮም የማዕከሉን 11ኛ አመት ምስረታ ምክንያት በማድረግ ከጳጉሜ በፊት ያሉትን 5 ቀናት ጨምሮ 5ቱን የጳጉሜ ቀናት በማካተት የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ለመተግበር ማቀዱን ሰምተናል፡፡በመሆኑም ታካሚዎች በጤና ተቋማት የታዘዘላቸው ማስረጃ በመያዝ በስልክ ቁጥር 0940 05 05 05 ወይም 0940 04 04 04 ተመዝግበው መመርመር ይችላሉ ሲል ማዕከሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *