loading
ዛማሊክ የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ አሸናፊ ሆነ፡፡

የ2018/19 የቶታል ካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ የመልስ ግጥሚያ ትናንት ምሽት ግብፅ ላይ ተካሂዷል፡፡

የፍፃሜው ጨዋታ ደግሞ ግብፁ ኤል ዛማሊክ እና የሌላኛዋ ሰሜን አፍሪካዊት ሀገር ሞሮኮ ተወካይ ሬነሳንስ ስፖርቲቭ ዴ ቤርካኔ መካከል ዛማሊክ በመለያ ፍፁም ቅጣት ምት 5 ለ 3 በመርታት በታኩ የመጀመሪያውን የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ አሳክቷል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች ባለፈው ሳምንት ሞሮኮ ላይ የመጀመሪያ ግጥሚያቸውን አድርገው፤ ቤርካኔ ባለቀ ሰዓት ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 መርታት ቢችሉም፤ በትናንት ምሽቱ የቦርጅ አል አረብ ስታዲየም ፍልሚያ ዛማሊክ በሜዳው በተመሳሳይ 1 ለ 0 ውጤት ድል አድርጓል፡፡ ማሃሙድ አላ ደግሞ ለግብፁ ቡድን የድሏን ጎል ከመረብ አገናኝቷል፡፡

ሁሉቱ ቡድኖች በደርሶ መልሱ ጨዋታ 1 ለ 1 አቻ መለያየታቸውን ተከትሎ፤ በተሰጠው የመለያ ፍፁም ቅጣት ምት የግብፁ ዛማሊክ 5 ለ 3 በማሸነፍ ለ16 ዓመታት የናፈቀውን አህጉራዊ ዋንጫ ከ2003 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ስሟል፡፡

ለአህጉራዊ ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ለፍፃሜ የደረሰው ቤርካኔ የመጀመሪያ ውጤቱን ባለማስጠበቁ ተሸንፏል፡፡ 

የፍፃሜ ጨዋታውን ኢትዮጵያዊው አርቢትር በአምላክ ተሰማ መርቶታል፡፡

ዛማሊክ የውድድሩ አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ የዋንጫ እና የ1.25 ሚሊዬን የአሜሪካን ዶላር ሽልማት ሲያገኝ፤ ቤርካ የ625 ሺ ዶላር አግኝቷል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *