loading
ዛሬ ምሽት በቻምፒዮንስ ሊግ ከምድብ አምስት እስከ ስምንት የሚገኙ ቡድኖች የምድብ አራተኛ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ

ዛሬ ምሽት በቻምፒዮንስ ሊግ ከምድብ አምስት እስከ ስምንት የሚገኙ ቡድኖች የምድብ አራተኛ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ

አርትስ ስፖርት 28/02/2011

በምሽቱ ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል ከምድብ አምስት በአልያንዝ አሬና ባየርን ሙኒክ ከኤኢኬ አቴንስ ይገናኛሉ፡፡ እዚሁ ምድብ ቤኔፊካ ከ አያክስ ይጫወታሉ፡፡ አያክስና ባ/ሙኒክ ምድቡን በእኩል ሰባት ነጥብ ይመሩታል፡፡ በስድስተኛው ምድብ በኢቲሀድ ማንችስተር ሲቲ ከ ሻክታር ዶኔስክ ጋር ሲፋለሙ ሊዮን ሆፈንየምን ያስተናግዳል፡፡ ሲቲ በስድስት፣ ሊዮን በአምስት ነጥቦች በምድቡ ቀዳሚና ተከታይ ናቸው፡፡ በምድብ ሰባት ደግሞ ሮማ ወደ ሩሲያ አቅንቶ ከሲኤስኬኤ ሞስኮው እንዲሁም ሪያል ማድሪድ ወደ ቼክ አቅንቶ ከቪክቶሪያ ፕለዘን ጋር የሚጫወቱ ይሆናል፡፡ ማድሪድና ሮማ በእኩል ስድስት ነጥቦች ምድቡን ይመሩታል፡፡ በመጨረሻው ምድብ ስምንት ደግሞ በአልያንዝ ስታዲየም ዩቬንቱስ ማንችስተር ዩናይትድን ያሰተናግዳል፤ ዩቬንቱስ ምድቡን በስድስት ነጥብ ሲመራ፣ ዩናይትድ በስድስት ነጥብ ይከተላል፡፡ አሮጊቷ ድል ምታደርግ አልያ አቻ የምትለያይ ከሆነ ወደ ቀጣዩ ዙር ታልፋለች፤ ፖል ፖግባ ወደ ቀድሞ ቤቱ መጥቶ የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡ ሮሜሉ ሉካኩ በጉዳት ምክንያት ጨዋታው ሊያልፈው እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል፡፡ እዚሁ ምድብ ቫሌንሲያ ከ ያንግ ቦይስ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል፡፡ ምሽት ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል ሲኤስኬኤ ሞስኮው ከ ሮማ እና ቫሌንሲያ ከ ያንግ ቦይስ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታዎች ምሽት 2፡55 ላይ ሲደረጉ ሌሎቹ በተመሳሳይ ምሽት 4፡00 ላይ ይከናወናሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *