ዛሬ የላባደሮች ቀን በኢትዮጵያ ለ44ኛ ጊዜ እየተከበረ ነዉ ፡፡
ዛሬ የላባደሮች ቀን በኢትዮጵያ ለ44ኛ ጊዜ እየተከበረ ነዉ ፡፡
በርካታ አገሮች ግንቦት አንድን የላብ አደሮች ቀን ወይም ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀን በማለት ያከብሩታል።
በሰሜን አሜሪካ የላብ አደሮች ቀን የሚከበረው በመስከረም ወር የመጀመሪያው ሰኞ ላይ ነው። በአገራችን ደግሞ በዛሬው ዕለት እየተከበረ ይገኛል፡፡
የዛሬው ዕለት ዓለም አቀፍ ቀን ሆኖ እንዲከበር የተወሰነበት ዋናው ምክንያት በ1986 በቺካጎ በተነሳው የሰራተኞች የስምንት ሰዓት ስራ እንዲከበር የተቀጣጠለው አድማ በፖሊሶች በተተኮሰ ጥይት 4 ሰዎች ለህልፈት በመብቃታቸው እንደሆነም ይነገራል፡፡