የህንድ የጎርፍ አደጋ ስጋት ህንድ ውስጥ የመሬት መንሸራተት ባስከተለው አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ40 በላይ ደረሰ::
አዲስ አበባ፣ነሐሴ4፣ 2012 የህንድ የጎርፍ አደጋ ስጋት ህንድ ውስጥ የመሬት መንሸራተት ባስከተለው አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ40 በላይ ደረሰ::
በደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል በአንድ የሻይ ማሳ ላይ በደረሰው በዚህ አደጋ እስካሁን የሟቾቹ ቁጥር 43 ደርሷል ነው የተባለው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው የመሬት መንሸራተት አደጋው መንስኤ በሀገሪቱ እየዘነበ ያለው ከባድ ዝናብ ሲሆን በአደጋው ሳቢያ ከ24 ሰዎች በላይ የገቡበት አልታወቀም፡፡ የሀገሪቱ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ የሚያደርጉት የጠፉ ሰዎችን የማፈላለግ ስራ በዝናቡ ምክንያት እንዳስተጓጎለበቸው ተናግረዋል፡፡
የህንድ የአየር ትንበያ ባለ ሙያዎች በደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል በምትገኘው የኬራላ ግዛት የዝናቡ ሁኔታ በቀጣዮቹ ቀናትም ተባብሶ እንደሚቀጥል በመግለፅ ህዝቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡ በህንድ ከግንቦት ወር መገባደጃ ጀምሮ እስካሁን ባለው ጊዜ ከዝናና ጎርፍ ጋር በተያያዘ ምክንያት በትንሹ 780 ሰዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ይፋ አድርገዋል፡፡