loading
የህክምና ኦክስጂን ማምረቻ እና ማከፋፈያ ማዕከል በጅግጅጋ ተመረቀ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27 ፣ 2013 የህክምና ኦክስጂን ማምረቻ እና ማከፋፈያ ማዕከል በጅግጅጋ ተመረቀ:: የሶማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማ ያስገነባውን የህክምና ኦክስጂን ማምረቻ እና ማከፋፈያ ማዕከል የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ በተገኙበት አስመርቋል።
በምርቃት ስነ-ስርአቱ ላይ ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን እና የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዩሱፍ መሀመድ ተገኝተዋል።

የማእከሉ መገንባት እንደ ክልል የነበረውን የህክምና ኦክስጂን እጥረትን እንደሚቀርፍ እና ከዚህ በፊት 622 ኪ/ሜ አዲስ አበባ ድረስ ይኬድ የነበረውን ርቀትና ወጪ የሚቀንስ መሆኑም ነው የተገለፀው። ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ በምርቃ ስነ-ስርአቱ እንደገለፁት የህክምና ኦክስጂኑ በዚህ ወቅት ስራ መጀመሩና መመረቁ በተለይ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ታማሚዎች ላይ እያጋጠመ ያለውን የመተንፈሻ ኦክስጅን እጥረትን በከፍተኛ ደረጃ ይቀርፋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ሐላፊ ዶ/ር ዩሱፍ መሐመድ በበኩላቸው ከክልሉ የቆዳ ስፋት አንፃር የህክምና ኦክስጅን ተደራሽነት ላይ የነበረውን ችግር እንደሚቀርፍ ጠቅሰው፣ ይህ አሁን ስራ የጀመረው የኦክስጅን ማምረቻ ማእከል በቀን ወደ 200 ሲሊንደር ማምረት ስለሚችልና የክልሉን የኦክስጅን ፍላጎት እንደሚሸፍን ገልፀዋል ሲል የክልሉ ማስሚድያ ኤጀንሲ ዘግቧል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *