loading
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በሀገሪቱ ተጥሎ የቆየውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አነሳ፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በሀገሪቱ ተጥሎ የቆየውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አነሳ፡፡ ምክር ቤቱ በስብሰባው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ በ63 ተቃውሞ በ21 ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ እንዲነሳ ወስኗል፡፡ ይህን ውሳኔ ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ ያላጠናቀቃቸው ጅምር ስራዎች ካሉ ይህ ውሳኔ ከተላለፈበት ከዛሬ ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ
አጠናቆ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት እንዲያደርግ ተወስኗል፡፡ በተመሳሳይ የፍትህ አካላት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ የጀመሯቸውን ጉዳዮች
በመደበኛው የፍትህ አሰጣጥ ስርአት እንዲያጠናቅቁም ነው የተወሰነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *