loading
የህግ ባለሙያ አካል ጉዳተኞች ማህበር በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ተመሰረተ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 የህግ ባለሙያ አካል ጉዳተኞች ማህበር በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ተመሰረተ::የህግ ባለሙያ አካል ጉዳተኞች ማህበር ምስረታ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ይፋ ተደረገ።

በማህበሩ ምስረታ ላይም የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ፣ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።በምስረታው ላይ የተገኙት ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ባስተላለፉት መልእክት፥ በማህበሩ መመስረት የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።

በቀጣይ ከማህበሩ ጋር በጋራ በመሆን ስራዎችን እንደሚሰሩ ቃል መግባታቸውን ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።የማህበሩ መስራች እና የቦርድ ሰብሳቢ የትነበርሽ ንጉሴ በበኩላቸው፥ የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ አካል ጉዳተኞች ማህበር ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የተቋቋመ ሙያዊ የአካል ጉዳተኞች ማህበር በመሆኑ የዛሬው ቀን ታሪካዊና ለአካል ጉዳተኞች ትልቅ ምዕራፍ እንደሆነ ተናግረዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *