loading
የሊቢያ መንግስት ሲርት ላይ ጥቃት የሚፈፅም ከሆነ ግብፅ ጣልቃ እንድትገባ ጄንራል ከሊፋ ሀፍታር ጠየቁ ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2012 የሊቢያ መንግስት ሲርት ላይ ጥቃት የሚፈፅም ከሆነ ግብፅ ጣልቃ እንድትገባ ጄንራል ከሊፋ ሀፍታር ጠየቁ ::በጄኔራል ከሊፋ ሀፍታር የምትተዳረው ምስራቃዊ ሊቢያ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አጉሊያ ሳልህ የሊቢያመንግስት ወደ ሲርት የሚያደርገውን ግስጋሴ ካላቆመ የግብፅ ድጋፍ ያስፈልገናል ብደለዋል፡፡በቅርቡ በተለያዩ ግንባሮች ድል እየቀናው የሚገኘው የጠቅላይ ሚስትር ፋይዝ አላሳራጅ ጦር በበኩሉስትራጂያዊ ቦታ የሆነችውን ሲርትን ሳንቆጣጠር መመለስ ብሎ ነገር የለም ብሏል፡፡አልጀዚራ እንደዘገበው ሳልህ በሰጡት መግለጫ ግብፅ የሚደርስብንን ጥቃት ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ መብቱ አላት ብለዋል፡:ሰሞኑን ግብፅ በሰጠችው መግለጫ ሊበያ ውስጥ ያለው የቱርክ ወታደራዊ እንቅስቃሴ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ታልቃ ለመግባ እገደዳለሁ ማለቷ የሚታወስ ነው፡፡የጄኔራል ከሊፋ ሀፍታ ጦር በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እውቅና የተሰጠውን የትሪፖሊን መንግስት በሃይል ለመጣል የጀመረው ዘመቻ አሁን ላይ በሽንፈት ሊደመደም ተቃርቧል የሚሉ ወገኖች ተበራክተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *