የሊቢያ መንግስት የትሪፖሊ አየር ማረፊያን አስመልሻለሁ አለ፡፡
አዲስ አበባ ፣ግንቦት 27፣ 2012 የሊቢያ መንግስት የትሪፖሊ አየር ማረፊያን አስመልሻለሁ አለ፡፡አለም አቀፍ እውቅና ያለው የጠቅላይ ሚኒስትር ፋይዝ አልሳራጅ መንግስት በጄኔራል ከሊፋ ሀፍታርጦር ተይዞ የነበረውን አየር መንገድ በውጊያ መልሶ መቆጣጠሩን ተናግሯል፡፡አልጀዚራ እንደዘገበው አየር መንገዱ በሀፍታር ሰራዊት ስር በመውደቁ የተነሳ እንደአወሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2014 ጀምሮ ከአገልግሎት ውጭ ሆኖ ነበር፡፡ከስድስት ዓመታት በፊት ትሪፖሊን ለመቆጣጠር አልመው ጦርነት ያወጁት ሀፍታር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ግንባሮች እየተሸነፉ ተቆጣጥረዋቸው የነበሩትን ቦታዎች ጥለው እያፈገፈጉ ነው ተብሏል፡፡
የሊቢያ መንግስት ወታራዊ ቃል አቀባይ የመከላከያ ሀይላችን አየር መንገዱን ሙሉ በሙሉ ነፃ አውጥቶታል ለዚህም ምስጋና ይገባዋል ብለዋል፡፡
በርካታ አስተያየት ሰጭዎች የሀፍታር ጦር መፍረክረክ የጀመረው ቱርክ ለትሪፖሊ መንግስት ወታደራዊ ድጋፍ ማድረግ ከጀመረች ወዲህ ነው ይላሉ፡፡
የጄኔራል ከሊፋ ሀፍታ ጦር በዋናነት በተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች፣ በግብፅ እና በሩሲያ ይደገፋል ተብሎ ይታመናል፡፡