loading
የላልይበላ በረራ ዳግም መጀመር ቱሪዝምን ለማነቃቃት ዘርፉ ያለው ሚና…

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቋርጦ የነበረውን የላልይበላ በረራ ዳግም መጀመሩ ተሰማ፡፡ አየር መንገዱ አሸባሪው የትሕነግ ቡድን በላልይበላ አውሮፕላን ማረፊያ ከፍተኛ ዝርፊያና ውድመት ማድረሱን ተከትሎ ነበር በረራውን ያቋረጠው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ግን የልደት በዓልን በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላልበይላ ለሚያከብሩ ምዕምናንና አካባቢውን ለሚጎበኙ ተጓዦች አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ይፋ አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥትም ዘረፋና ውድመት የደረሰበትን የላልበይላ አየር ማረፊያ በአፋጣኝ ጥገና ተደርጎለት ሥራ እንዲጀምር ከፍተኛ ጥረት አድርጓል ነው የተባለው፡፡
መንግሥት አየር መንገዱ በአፋጣኝ ተጠግኖ ለአገልግሎት ብቁ እንዲሆን የወሰደው እርምጃ በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ የሚከበረውን የገና በዓል ለመታደም ለሚጓዙ ሰዎች መልካም አጋጣሚ መሆኑና የአካባቢውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ዳግም ለማነቃቃት ወሳኝ ድርሻ እንዳለው ተነግሯል፡፡ ወራሪው የሕወሃት ቡድን በወገን ጦር ሽንፈት ገጥሞት አካባቢውን ሲለቅ በላልበይላ አየር ማረፊያ ከፍተኛ ውደመትና ዘረፋ ማድረሱ ይታወቃል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *