loading
የላልይበላ ቤተ ጎልጎታ ሚካኤል ከ700 ሺህ ዶላር በላይ በሆነ ወጪ ተጠግኖ ተመረቀ

የላልይበላ ቤተ ጎልጎታ ሚካኤል ከ700 ሺህ ዶላር በላይ በሆነ ወጪ ተጠግኖ ተመረቀ

አርትስ 12/03/2011

ከላልይበላ 11ዱ ፍልፍል አብያተ ክርስትያናት ውስጥ አንዱ የሆነው የቤተ ጎልጎታ ሚካኤል ከአሜሪካ አምባሳደር ፈንድ እና ከአለም ሞኑመንት ፈንድ በተገኘ ድጋፍ ነዉ የተጠገነዉ፡፡

በምርቃት ስነ-ስርአቱ ወቅት እንደተነገረው ቅርሶች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ቀድሞ ለመከላከል እንዲቻል የቅርስ ጥገና እና እንክብካቤ ስራን በመከታተል ልዩ ትኩረትመስጠት ይገባል።

በቤተ ጎልጎታ ሚካኤል ውስጥ የታዩ የመሰንጠቅ፣ የጣራ ማፍሰስ እና ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ችግሮችን ለመከላከል እና ቅርሶቹን ለማቆየት በሚደረገው ጥረትምውጤታማ እና የራስ አቅምን ያጎለበተ እንደነበር ባለሙያዎች ተናግረዋል።

በጥቅምት 2009 ዓ.ም የተጀመረው የጥገና ፕሮጀክት ከዚህ በፊት በቤተ ገብርኤል-ሩፋኤል እና ቤተ ጎልጎታ-ሚካኤል ቤተክርስትያናት የተገኙ ተሞክሮዎችን መሰረትበማድረግ የተሰራ ነው፡፡

በቀጣይም በመጠለያ ስር በሚገኙ ቤተክርስትያናት ላይ ጥገና በማድረግ ተከልለው የሚገኙትን ጊዜያዊ የብረት መጠለያዎችን ማንሳት የሚያስችል ፕሮጀክት ለመጀመር በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ቅርስ ጥናት እና ጥበቃ ባለስልጣን ገልጿል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *