loading
የልብ ደም ስር መጥበብ ህክምና (ፒሲአይ) የህክምና አገልግሎት ሊሰጥ መሆኑን ማዕከሉ አስታወቀ፡፡ የ

የልብ ደም ስር መጥበብ ህክምና (ፒሲአይ) የህክምና አገልግሎት ሊሰጥ መሆኑን ማዕከሉ አስታወቀ፡፡
የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በጋራ ያስገነቡት የልብ ህክምና ማዕከል ከዛሬ ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት የደም ስር መጥበብ ችግር ላለባቸው ታካሚዎች የፒሲአይ ህክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታዉቋል፡

ማዕከሉ በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግቢ የሚገኝ ሲሆን ህክምናው ከኮሪያ በሚመጡ የህክምና ቡድን አባላትና በማዕከሉ ባለሙያዎች ይሰጣል፡፡

ህክምናው የሚደረግላቸው ታካሚዎች በማዕከሉ ቀጠሮ ተይዞላቸው ሲጠባበቁ የነበሩ መሆናቸውን ማዕከሉ ገልጿል፡፡

ይህ ህክምና ለዘጠነኛ ጊዜ የሚሰጥ ሲሆን በዚህ ዙር የፒሲአይ ህክመና ብቻ እንደሚሰጥም ታውቋል፡፡
ቀደም ባሉት ዙሮች ከዘጠና በላይ የሚሆኑ ታካሚዎች ይህን አገልግሎት ማግኘታቸውን ከማዕከሉ ማወቅ ችለናል፡፡

የፒሲአይ ህክምና አገልግሎት በጣም ውድ ከሆኑ የልብ ህክምና አገልግሎቶች አንዱ ሲሆን በግል ሆስፒታሎች ከመቶ ሺ ብር በላይ ወጪ የሚጠይቅ ነው ተብሏል፡፡

ምንጭ ፤-የማእከሉ ድረ ገጽ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *