የሎጂስቲክ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት ይደረጋል አሉ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ
አርትስ 27/02/2011
ሚኒስትሯ ይህንን ያሉት የሀገሪቱ ሎጅስቲክ ያለበትን ሁኔታ ለመመልከት የሞጆ ደረቅ ወደብን በጎበኙበት ወቅት ነው፡፡ የባህርትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ባለስልጣን ዋናስራ አስፈፃሚ አቶ ሮባ መገርሳ እንዲሁምየሚመለከታቸው ኃላፊዎች ለሚኒስትሯ ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡
እንደ ትራንስፖርት ሚኒስቴር መረጃ የሞጆ ደረቅ ወደብ ያሉበትን ችግሮቹን ለመፍታት ከአዳዲሶቹ አመራሮች ብዙ ስራ ይጠበቃል ፡፡
ሚኒስትሯ በዘርፉ የሚታዩትን ችግሮች በዘላቂነት ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል፡፡
በጉብኝቱ የተሳተፉት የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለሀገራዊ እድገት ግንባታ በየዘርፋችን መረባረብ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡