የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአገራዊ ምክክሩን በሃላፊነት የሚመሩትን የ11 እጩ ኮሚሽነሮችን ሹመት አጸደቀ።
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 ምክር ቤቱ በዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባት ለመፈጠር ያስችላል የተባለው የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265 /2014 ማጽደቁ ይታወሳል። በዚህም መሰረት አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑን የሚመሩት 11 ኮሚሽነሮች ለመለየት ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በተለያዩ የጥቆማ ዘዴዎች ከ600 በላይ ሰዎች ተጠቁመዋል።
ከተጠቆሙት ግለሰቦች መካከል 42ቱ አዋጁን መሰረት ተደርጎ መለየታቸውና ኅብረተሰቡም አስተያየት እንዲሰጥባቸው መደረጉ ተገልጿል። በመሆኑም አገራዊ ምክክሩን ለመምራት የ11 እጩዎች ዝርዝር ለውሳኔ ቀርቦ ምክር ቤቱም ዛሬ ባካሄደው ሁለተኛ አስቸኳይ ስብሰባው በአምስት ድምጽ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ የኮሚሽሮቹን ሹመት አጽድቋል። በዚህም መሰረት ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ሰብሳቢ፣ ወይዘሮ ሂሩት ገብረስላሴ ምክትል ሰብሳቢ ሆነው
ሲሾሙ ቀሪዎቹ 9 እጩዎች በኮሚሽነርነት ተሾመዋል፡፡