loading
የመመስረቻ መስፈርት አሟልተው የተገኙ ስምንት አዳዲስ ባንኮች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ተሰጣቸው፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2014 የመመስረቻ መስፈርት አሟልተው የተገኙ ስምንት አዳዲስ ባንኮች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ተሰጣቸው፡፡
በፋይናንስ ዘርፉ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ለውጦችን ተከትሎ በርካታ ባንኮች የመመስረቻ ፈቃድ ለማግኘት ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንክ ቁጥጥር ዳይሬክተር ፍሬዘር አያሌው ባንክ ለመመስረት የሚያስፈልገው ዝቅተኛ የካፒል መጠን ከ500 ሚሊዮን ወደ 5 ቢሊዮን ብር ከፍ መደረጉን አስታውሰው አጠቃላይ መስፈርቱን ላሟሉ ፈቃድ እየተሰጠ መሆኑን ጠቅሰዋል። በዚህ መሰረት የመመስረቻ ፈቃድ ከጠየቁ 25 አዳዲስ ባንኮች መካከል ብሔራዊ ባንክ ያወጣውን መስፈርት አሟልተው ለተገኙ 8 ባንኮች ፈቃድ መስጠቱን ተናግረዋል።


በብሄራዊ ባንክ ፈቃድ ካገኙ ስምንት ባንኮች በተጨማሪ 3 ባንኮች ፈቃድ የማግኘት ሂደቱን እያጠናቀቁ ሲሆን ሶስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውሰጥ እንደሚያገኙም ገልጸዋል።
ብሔራዊ ባንክ ከቅድመ ማመልከቻ ሂደት ጀምሮ ፈቃድ ከተሰጠ በኋላ ቁጥጥር እንደሚያደርግ ገልጸው  የምስርታ ሂደቱ ካልተሳካ ለባለአክሲዮኖች ገንዘባቸው ተመላሽ ይሆናል ብለዋል።


በተመሳሳይ አነስተኛ የገንዘብ ተቋማት ወደ ባንክ እንዲሸጋገሩ በ2012 ዓ.ም ብሄራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ መሰረት መስፈርቱን ያሟሉ 3 አነስተኛ የገንዘብ ተቋማት ወደ ባንክነት መሸጋገራቸውን ገልጸዋል። ሌሎች ሁለት አነስተኛ የገንዘብ ተቋማት ደግሞ መስፈርቱን አሟልተው ፈቃድ ለማግኘት በሂደት ላይ
ናቸው ተብሏል፡፡ ከ120 ሺህ በላይ ዜጎች ቀጥተኛ የስራ እድል የፈጠረው የባንክ ዘርፍ አዳዲስ ባንኮች ወደ ስራ ሲገቡ አማራጭ አገልግሎትን ከማቅረብና የስራ እድል ከመፍጠር አንጻር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *