loading
የመስኖ ዘርፍ ቴክኖሎጂ ለማሳደግ እና ክህሎት ያለው የሰው ሀይል ለማፍራት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2014 የመስኖ ዘርፍ ቴክኖሎጂ ለማሳደግ እና ክህሎት ያለው የሰው ሀይል ለማፍራት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ፡፡ ስምምነቱ የተፈረመው በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መካከል ነው፡፡ ይህ ስምምነት የተናበበና የተቀናጀ የአሠራር ሥዓርት በመዘርጋት የሀብትና የጊዜ ብክነትን በማስቀረት ብቁ የሰው ኃይል በማፍራት በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በሚተገበሩ ፕሮግራሞች ላይ እንዲሳተፉ ያግዛል ነው የተባለው፡፡


የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሐመድ በዘርፉ የሚሳተፈው የሰው ኃይል በቂ ግንዛቤ ያለውና የውሃ መሰረተ ልማትን በአግባቡ ሥራ ላይ ለማዋል መግባቢያ ሰነዱ መፈረሙን ተናግረዋል፡፡ የመስኖ ዘርፍ ቴክኖሎጂን ለማሳደግ፣ ክህሎት ያለው የሰው ሀይል ለማፍራት፣ በመስኩ ለሚሰማሩ ዜጎችን የሙያ ደህንነት ለመጠበቅ የስምምነት ሰነዱ ወሳኝ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ናቸው፡፡


የየመግባቢያ ሰነዱ ፕሮጀክት አፈጻጸም ውጤታማነትን በማሳደግ ህብረተሰቡ ከዘርፉ ልማት ተጠቃሚ እንዲሆንና ትልቅ ፋይዳ አለው ነውነ የተባለው፡፡ከዚህም ባሻገር ለስራ ፈላጊ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር የሃገሪቱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያ ዕድገት የሚጠበቅበትን ሚና ለመወጣት እንደሚያስችልም በፊርማ ሥነ- ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *