የመንግስታቱ ድርጅት የኤርትራን ማዕቀብ በነገው ዕለት ሊያነሳ ነው
አርትስ 04/03/2011
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኤርትራ ላይ ላለፉት 10 ዓመታት ጥሎት የነበረውን ማዕቀብ ለማንሳት ውሳኔዎች እንደሚያስተላልፍ ተገለፀ፡፡
ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ያደረገችውን የሰላም ስምምነት እንዲሁም ከጅቡቲ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል ያደረገችውን ጥረት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው ማዕቀቡን ለማንሳት የፀጥታው ምክር ቤት አባላት ተደራድረው የጨረሱት፡፡
ሮይተርስ የድርጅቱን ዲፕሎማቶች ጠቅሶ እንደዘገበው ማዕቀቡን ለማንሳት በእንድሊዝ የቀረበውን ረቂቅ 15 የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባላትያለልዩነት እንደሚቀበሉት ይጠበቃል፡፡
ኤርትራ የሶማሊያውን አልሸባብ ለሚባለው ቡድን እገዛ ታደርጋለች በሚል እንደአውሮፓዊያኑ አቆጣተር በ2009 አ.ም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማዕቀቡን እንደጣለባት ይታወሳል፡፡