loading
የመድሀኒት እጥረትን በቋሚነት ለመፍታት የሚያስችል የኤሌክትሮኒክ የመድሀኒት ምዝገባ ና ቁጥጥር ሥርዓት መጀመሩን ባለሥልጣኑ አስታወቀ፡፡

የመድሀኒት እጥረትን በቋሚነት ለመፍታት የሚያስችል የኤሌክትሮኒክ የመድሀኒት ምዝገባ ና ቁጥጥር ሥርዓት መጀመሩን ባለሥልጣኑ አስታወቀ፡፡

በኤሌክትሮኒክስ የመድሀኒት ምዝገባ ና ቁጥጥር ሥርዓት መጀመሩ ይፋ ሲደረግ የተገኙት የጤና ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን  የፌዴራል ምግብና መድሀኒት ቁጥጥር  ባለስልጠን የሚሰጣቸዉን አገልግሎቶች እጅግ ወሳኝ በመሆናቸዉ አስተማማኝ መሆን እንደሚጠበቅባቸዉ  ተናግረዋል ፡፡

ዶክተር አሚር መስሪያቤታቸዉ  ሊተገብራቸዉ በእቅድ ከያዛቸዉ አጀንዳዎች መካከል አንዱ የሆነዉ የመረጃ አብዮት ነዉ  በኤሌክትሮኒክ የመቆጣጠሪያ ሥርዓት የሚከናወኑ የመድሀኒት ምዝገባ ና ቁጥጥር ሥርዓት ደግሞ ለዚህ ወሳኝ ነዉ ብለዋል፡፡

የፌዴራል የምግብና መደሀኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሪት ሄራን ገርባ በበኩላቸዉ በሀገራችን የሚታየዉን የመድሀኒት እጥረት በቋሚነት ለመፍታት እንዲቻል ፤ የመድሀኒት ምዝገባ ሥርዓቱን የተቀላጠፈና ምቹ ለማድረግ  መሠረታዊ ለዉጥ ማምጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህ ዘመናዊ የአሠራር ሥርዓት ተዘርግቷል ብለዋል፡፡

የኤሌክትሮኒክ የመቆጣጠሪያ ሥርዓቱ ህገወጥ መድሀኒቶችን የመለየትና የማወቅ ፣የመድሀኒት ግዥን፣የምግብና መድሀኒት ብቃት ማረጋገጫን ማከናወን፣ የምግብ ምዝገባ እንዲሁም የመድሀኒት ምዝገባን ማከናወን ሲሆን ሁሉንም አገልግሎቶች በቀላሉ ካሉበት ቦታ በመሆን በኦንላይን ማከናወን ያስችላል፡፡

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *