የመጀመሪያው የህፃናት የወባ ክትባት በማላዊ ሊጀመር ነው፡፡
የመጀመሪያው የህፃናት የወባ ክትባት በማላዊ ሊጀመር ነው፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት እንዳስታወቀው ክትባቱ በአፍሪካ ተግባራዊ ከሆነ በወባ በሽታ የሚሞቱትን ህፃናት ህይዎት ይታደጋል፡፡
በሙከራ ደረጃ እንደታየው በአህጉሪቱ ያሉ ህፀናት ክትባቱን በተገቢው መንገድ ካገኙ በወባ ከሚሞቱ 10 ህፀናት አራቱን ማዳን ይቻላል፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው ማላዊ የወባ ከትባትን ለህፃናት በሙከራ ደረጃ ለመስጠት ዝግጂቷን ጨርሳለች፡፡
ከ3 አስርት ዓመታት ያላነሰ ጊዜ እና 1 ቢሊዮን ዶላር ወጭ የተደረገበት የወባ ህመም መከላከያ ክትባት በማላዊ በጋና እና በኬንያ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡
እነዚህ 3 ሀገራት የመጀመሪያዎቹ ሆነው የተመረጡበት ምክንያት በአፍሪካ ደረጃ በወባ ስርጭት ቀዳሚውን ስፍራ ይዘው በመገኘታቸው መሆኑም ተነግሯል፡፡
በአፍሪካ በየዓመቱ ከ250 ሺህ በላይ ህጻናት በወባ መሽታ እንደሚሞቱ የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት ያሳያል፡፡
ከፕሮቲን ቅንጣት የተዘጋጀው ይኸው ክትባት ለአምስት ዓመታት ያህል በ15 ሺህ ሰዎች ላይ ተሞክሮ ውጤታማ መሆኑ ስለተረጋገጠ ነው ስራ ላይ የሚውለው፡፡
ክትባቱ የሚሰጠው እድሜያቸው በ5 ወር እና በ2 ዓመት መካከል ለሚገኝ ህፃናት መሆኑንም ዘገባው አመላክቷል፡፡
መንገሻ ዓለሙ