የመጪው ክረምት ዝናብ ለሕዳሴው ግድብ በረከት::
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16፣ 2013 የመጪው ክረምት ዝናብ ለሕዳሴው ግድብ በረከት የመጪው ክረምት ዝናብ ለሕዳሴው ግድብ የውሃ ሙሌት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ተባለ:: ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ያለፈውን በልግና የመጪውን ክረምት የአየር ሁኔታ ግምገማና ትንበያ ይፋ አድርጓል። በመጪው ክረምት የአየር ጠባይ አዝማሚያ ትንበያው የአገሪቱ የምዕራብ አጋማሽ አብዛኞቹ ቦታዎች ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚያገኙና በጥቂት ቦታዎችም መደበኛ ዝናብ እንደሚኖር አስታውቋል።
የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለም በክረምቱ የሚጠበቀው ዝናብ መጠንና ስርጭት ለግድቡ ውሃ ሙሌት እውን መሆን ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ገልጸዋል። በተጨማሪም የክረምቱ ዝናብ ዘንድሮ ለሚካሄደው ሦስተኛው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዕቅድ ስኬታማነት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውተ ጠቁሟል። የክረምቱ ዝናብ ግብርናና ሌሎች የልማት ስራዎችን ለማከናወንም የተለየ ዕድል ይፈጥራል ነው የተባለው፡፡ ሚኒስትሩ ሁለተኛውን ዙር የሕዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት ዕውን ለማድረግ የዘርፉ ባለሙያዎች ቀን ከሌሊት እየተጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።