loading
የማዕከላዊ አፍሪካ ዜጎች ወደጎረቤት ዲሞክራቲክ ኮንጎ መጠለያ ፍለጋ እየተሰደዱ ነው ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ጥር 21፣ 2013 የማዕከላዊ አፍሪካ ዜጎች ወደጎረቤት ዲሞክራቲክ ኮንጎ መጠለያ ፍለጋ እየተሰደዱ ነው ተባለ፡፡ ስደተኞቹ ቀያቸውን ጥለው የሚሰደዱት በሀገሪቱ ነፍጥ አንግበው ከሚዋጉ ሚሊሻዎች ጥቃት ህይዎታቸውን ለማዳን ሲሉ ነው፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው በአሁኑ ወቅት ከማዕከላዊ አፍሪካ ወደ ጎረቤትረ ዲሞክራቲክ ኮንጎ የተሰደዱ 30 ሺህ ዜጎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖራሉ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤት ለስደተኞቹ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ በርካታ እንቅፋቶች እንደገጠሙት ተናግሯል፡፡ የድጋፍ አቅርቦት እጥረት መኖሩ አንድ ችግር ሆኖ በሌላ በኩል ደግሞ የተገኘውን መጠነኛ አቅርቦት ለማዳረስ የፀጥታ ጉዳይም ሌላው እንቅፋት ነው ተብሏል፡፡ ባናጋሶ በተባለው የሀገሪቱ አካባቢ ባለፈው ጃኑዋሪ 3 የተቃዋሚ ጥምር ሃይሎች ያደረሱት ጥቃት በርካታ ሰዎች የተፈናቀሉበት እንደሆነም በሪፖርቱ ተመልክቷል፡፡ ማዕከላዊ አፍሪካ በተቃዋሚ ሃይሎችና በመንግስት መካከል በሚደረግ ውጊያ በርካታ ሰዎች ህይዎታቸው ከማለፉም ባሻገር በሀገሪቱ ከፍተኛ ስደትና አለመረጋጋት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *