የማዳጋስካሩ ፕሬዝዳንት የመጀመሪያውን ዙር ምርጫ ውድድር ተሸነፉ
አርትስ 20/03/2011
ከአሁን በፊት ማዳስካርን በፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በመጭው ምርጫ የድሉ ባለቤት ለመሆን ተፋጠዋል፡፡
አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው አሁን ላይ ሀገሪቱን እየመሩ ያሉት ፕሬዝዳንት ሄሪ ራጃወናሪማም ፒያኒና በመጀመሪያው ዙር ምርጫ 8.82 በመቶ ድምፅ ብቻ ነው ያገኙት፡
የቀድሞዎቹ ፕሬዝዳንቶችም ቢሆኑ 50 በመቶ ድምፅ ሳያገኙ በመቅረታቸው ነው ምርጫው ወደ ሁለተኛ ዙር ያመራው፡፡
ማርክ ራቫሎማናና 35.35 በመቶ አንድሪ ራጆሊና ደግሞ 39.23 በመቶ የሆነ ድምፅ በማግኘት በስራ ላይ ያሉትን ፕሬዝዳንት ከውድድሩ ውጭ አድርገዋቸዋል፡፡
ሁሌኛው ዙር ማዳስካር ፕዝዳንታዊ ምርጫ በመጭው ታህሳስ ወር እንደሚካሄድ ሀገሪቱ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ይፈፋ አድርጓል፡፡
የፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ጂያን ኤሪክ ራኮቶዋሪሶዋ የወቅቱ ፕሬዝዳንት በቀድሞወቹ መሪወች መሸነፋቸው ማዳስካር ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ማካሄድ እንምትችል ማሳያ ነው ብለዋል፡፡