loading
የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኢኩዋስ በማሊ ላይ የጣለውን ማእቀብ ያነሳል ተብሎ ይተጠበቃል::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኢኩዋስ በማሊ ላይ የጣለውን ማእቀብ ያነሳል ተብሎ ይተጠበቃል:: ማሊ ማእቀቡ የተጣለባት ባለፈው ወር በፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቡበከር ኬታ ላይ የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ ነው፡፡ መፈንቅለ መንግስቱ ከተካሄደ በኋላ ሀገሪቱ ወደ ሲቪል አስተዳደር እንድትመለስ ሲካሄድ የነበረውን ድርድር በበላይነት የመራው ኢኩዋስ ማእቀቡ ይነሳ አይነሳ በሚለው ጉዳይ ላይ ለመወሰን ለዓርብ ቀጠሮ ይዟል ተብሏል፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ጄኔራሎቹ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ባይስደማሙም የተመሰረተው የሽግግር መንግስቱ ተልእኮውን ሲያጠናቅቅ ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድና የሲቪል መንግስት ለመመስረት በመስማማቱ ነው ማእቀቡ ሊነሳ ይችላል የተባለው፡፡

የድርድሩ መሪ የቀድሞው የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት ኩድላክ ጆናታን ባማኮ ውስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በማሊ ላይ የተጣለውን ማእቀብ ለሀገሪቱ እንደ መጥፎ እድል የሚቆጠር ነው ብለዋል፡፡ መፈንቅለ መንግስት አድራጊዎቹም ህዝባዊ መንግስት ለመመስረት ከተስማሙ በኋላ ኢኩዋስ ማእቀቡን እንዲያነሳላቸው ጥያቄ አቅርበዋለው፡፡ ፕሬዚዳንት ኬታ በታማኝ ጄኔራሎቻቸው ከስልጣን ወርደው ለአስር ቀናት ያህል በእስር ከቆዩ በኋላ ተለቀው ለህክምና ወደ ተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች መጓዛቸው ይታወሳል፡፡ ኢኩዋስ ከፕሬዚዳንቱ ጋር በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞ የማሊ ባለ ስልጣናትም ከእስር እንዲለቀቁ
ጥሪ አቅርቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *