loading
የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) አባል ሀገራት መሪዎችም የማሊ ወታደሮች የሀገሪቱን ስልጣን መቆጣጠራቸውን አወገዘ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 15፣ 2012 የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) አባል ሀገራት መሪዎችም የማሊ ወታደሮች የሀገሪቱን ስልጣን መቆጣጠራቸውን አወገዘ::በወቅታዊ የማሊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ አስቸኳይ ስብሰባውን ያደረገወ የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ አባል ሀገራት (ኢኮዋስ) የማሊወታደሮች ፕሬዚዳንት ቡበከር ኬታን በቁጥጥር ስር አውሎ የሀገሪቱን ስልጣን መቆጣጠራቸውን አወገዟል፡፡

ኢኮዋስ በትላንትናው ዕለት ባደረገው የቪድዮ ስብሰባ ፕሬዝዳንቱ ቡበከር ኬታና በእስር የሚገኙ ባለስልጣናት በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ማስተላለፉ ተሰምቷል ፡፡ይህንን ተከትሎም ልኡኩ በከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የሰላም አስካባሪ ልኡክ በቦታው እንደሚልክ ነው ያስታወቀው፡፡

በቪድዮ አማካኝነት በተደረገው ስብሰባ የቡድኑ መሪ የሆኑት መሃመዲ ኢሱፉ የቡቡከር ኬታ መንግስት ዳግም እንዲመሰረት ሀገሪቱ ቀድሞ ወደነበረችበት ሰላሟ እንድትመለስ የሚገልፅ የአቋም መግለጫ ያወጣ ሲሆን ፤ የቡበከር ኬታና የሌሎች ባለስልጣናት ደህንነት እንደሚያሳስበው መገልጹን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል፡፡ቡበከር ኬታን በቁጥጥር ስር ያዋሉት ወታደሮች በበኩላቸው ስልጣን ለመያዝ ፍላጎት እንደሌላቸው በመግለፅ ነገር ግን ሀገሪቱን የማረጋጋት ስራ ለመስራት አስበው ድርጊቱን መፈፀማቸውን ገልፀዋል፡፡

ሆኖም የአፍሪካ ህብረት የማሊ የቀድሞ ቅኝ ገዢ ፈረንሳይ እና ጀርመንን ጨምሮ የወታደሮቹን እርምጃ ተቃውመውታል፡አሁኑ ሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነ ውጥረት ውስጥ የምትገኝ ሲሆን አንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎችም ከእንቅስቃሴ ተቆጠበዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *