loading
የሞሳድ ሹም በአቡዳቢ

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 13፣ 2012 የሞሳድ ሹም በአቡዳቢ የእስራኤሉ ሞሳድ የስለላ ድርጅት ሀላፊ በደህንነት ዙሪያ ለመወያየት አቡዳቢ ገብተዋል::
ሀላፊው ዮሲ ኮኸን እስራኤል እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የዲፕሎማሲ ስምምነት ከተፈራረሙ ወዲህ አቡዳቢን የጎበኙ የመጀመሪያው ባለ ስልጣን ሆነዋል፡፡

ኮኸን ከኤሜሬቶች የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሼክ ታኑም ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ሁለቱ ሀገራትበደህንነት እና ፀጥታ ዙሪያ በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል ተብሏል፡፡ ከዚህም በሻገር በሌሎች የጋራ የሆኑ ጉዳዮች እና በቀጠናው ሰላምና ልማት ዙሪያ እንዲሁም ኮሮናቫይረስን በጋራ ለመከላከል በሚያስችሉ ጉዳዮችም ተወያይተዋል፡፡

የአቡዳቢ ከቴል አቪቭ ጋር የተፈራረመችውን አዲስ የዲፕሎማሲ ግንኙነት አንዳንድ የአረብ ሀገራት እንደ ክህደት ቢቆጥሩትም በበርካታ ሀገራት ዘንድ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ ሁለቱ ሀገራት የተፈራረሙት የዲፕሎማሲ ስምምነት እስራኤል በዌስት ባንክ የፍልስጤም ይዞታዎችን ወደ ራሷ ለማስገባት የምታደርገውን እንቅስቃሴ ያስቆማል ቢባልም ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታኒያሁ ግን እቅዱ የዘገያል እንጅ አይቀርም ማለታቸው ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *