loading
የሠላምና የወዳጅነት ውድድር አይካሄድም ተብሏል

“የሠላም እና የወዳጅነት” ጨዋታ ከሚያዚያ 3 ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ኢትዮጵያ ፣ ጂቡቲ ፣ ሶማሊያ እና አዘጋጇ ሀገር ኤርትራ የሚሳተፉበት ውድድር እንደሚደረግ የተነገረ ቢሆንም፤ ሲከር ኢትዮጵያ አገኘሁት ባለችው መረጃ ውድድሩ እንደተሰረዘ ነው ።

ለውድድሩ መቅረት ምክንያቱ ምን እንደሆነ ግን የተገለፀ ነገር የለም ተብሏል።

ውድድሩ እንደማይካሄድ መረጋገጡን ተከትሎ ያለፉትን 15 ቀናት መቀመጫውን ሀራምቤ ሆቴል በማድረግ፤ 25 ተጫዋቾችን በመያዝ በአሰልጣኝ ዮሴፍ ተስፋዬ እየተመራ፤ ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘው ከ20 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፤ በምትኩ አንድ የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርግ እንደሚችል ታውቋል።

ፌዴሬሽኑ ውድድሩ መቅረቱን ተከትሎ ቡድኑ ከመበተን አንድ የወዳጅነት ጨዋታ እንዲያደርግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ሰምቻለው የምትለው ሶከር ኢትዮጵያ አዲስ አበባ እንደሚካሄድ በታሰበው በዚህ የወዳጅነት ጨዋታ ታጋጣሚዋ ሀገር ጅቡቲ እንደምትሆን፤ ቀኑ እና ሰዓቱም ወደ ፊት እንደሚገለፅ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *