loading
የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ከአንድ ሚሊዮን 151 ሺህ ብር በላይ ቁሳቁስ ለተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ

አርትስ 02/02/2011

የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ባለቤትና ሠራተኞች ድጋፍ ያደረጉት በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን አዋሳኝ ወረዳዎች መካከል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ነው።

ከአንድ ሚሊዮን 151 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የምግብና የአልባሳት ድጋፉን በመጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው ለሚገኙ ወገኖች ያስረከቡት የዩኒቨርሲቲው ነቀምቴ ካምፓስ ዲንና የባለሀብቱ ተወካይ አቶ ወንድሙ ቀኖ ናቸው፡፡

ተወካዩ ድጋፉን ዛሬ ለምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደር ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት የተደረገው እርዳታ ብርድ ልብስ፣ አልባሳት፣ ፓስታ፣ ማካሮኒና የተለያዩ የሕጻናት ምግቦችን ያካተተ ነው፡፡

” እርዳታው የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ አይደለም ” ያሉት አቶ ወንድሙ ተፈናቃዮቹ መልሰው እስኪቋቋሙ ድርስ በባለሀብቱ በኩል የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

ኢዜአ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *