የሰላም ሚኒስትሯ የሲዳማና የወላይታ አባቶችን አመሰገኑ
የሰላም ሚኒስትሯ የሲዳማና የወላይታ አባቶችን አመሰገኑ
አርትስ 10/03/2011
ትናንት “ፍቅር በደልን አይቆጥርም ” በሚል መርህ በሲዳማና በወላይታ ሕዝቦች መካከል ያለውን ትስስር ለማጠናከር የሚያግዝ የዕርቅና የሰላም ኮንፈረንስ በሀዋሳ ከተማ በሲዳማ ባህል አዳራሽ ተካሂዷል።
በኮንፈረንሱ ላይ የተገኙት የደኢህዴን ሊቀ መንበርና የኢፌደሪ የሠላም ሚኒስቴር ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪሀት ካሚል፥ በሲዳማና በወላይታ ሕዝቦች መካከል ሰላም ሰፍኖ ዕርቅና የሠላም ኮንፈረንስ እንዲካሄድ ትልቅ አስተዋፅኦ የነበራቸውን አባቶች አመስግነዋል፡፡
ሰላም በእያንዳንዳችን ልቦና እና ቤት የሚገኝ በኛው ጥበቃ የሚጎለብት በመሆኑ ልንጠብቀው ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ወጣቶች ሰላምን ከሚያደፈርሱ ቆስቋሽ ድርጊቶች እንዲጠበቁም አሳስበዋል፡፡
በዕርቁ ሥነ ሥርዓት ላይ ከሲዳማና ወላይታ ዞን የተወጣጡ የኃይማኖት መሪዎችና አባቶች፣ ከሁለቱም ዞኖች የተወጣጡ የባህል ሽማግሌዎችና ወጣቶች፣ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የኦሮሞ አባ ገዳዎች እና ጥሪ የተደረገላቸዉ ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡