loading
የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ዝግጁ ነኝ ብሏል፡፡

የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ ዝግጁ ነኝ ብሏል፡፡

በሱዳን ከወራት ህዝባዊ አመፅ በኋላ የመጣው ለውጥ አሁንም የህዝቡን ፍላጎት የሚመለስ አይደለም በማለት ሰልፈኞቹ በሲቪሎች የሚመራ የሽግግር መንግስት ካልተቋቋመ ትግላች ይቀጥላል እያሉ ነው፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው የሱዳን የባለሞያዎች ማህበር በመከላከያ ሀይሉ ጥበቃ የሚደረግለት የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት ጠይቆ ይህ ካልሆነ ግን የትኛውንም አይነት ሰላማዊ ተቃውሞ እንቀጥላለን ብሏል፡፡

የአልበሽርን ከስልጣን መወገድ ተከትሎ አዲስ የተቋቋመው ምክር ቤት ቃል አቀባይ እንዳሉት የጦር ሀይሉ  የሲቪል መንግስ ለመመስረት የሚያስችል የሽግግር ካውንስል ለማቋቋም ዝግጁ ነኝ ብሏል፡፡

ለሁለት ዓመታት ሀገሪቱን እንዲመራ የተቋቋመውን ወታደራዊ ምክር ቤት በበላይነት እንዲመሩ ቃለ መሀላ የፈፀሙትን አዋድ ኢብን  አውፍ ከስልጣን ተነስተው በምትካቸው ሌተናል ጄኔራል አብደልፈታህአልቡረሃንንተ ሾመዋል፡፡

የደህንነት ሀላፊው በገዛ ፈቃዳቸው ከስልጣናቸው መልቀቃቸውን ተከትሎም ምክር ቤቱ ሌተናል ጄኔራል አቡበከር ሙስጠፋን

በቦታቸው ተክቷል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *